top of page

Wisdom Well September 2025



ree


Dear Reader,


Thank you for reaching out. It takes courage to admit when we need help. Feeling overwhelmed it a universal human experience. This experience is often exasperated as a result of the fast-paced modern life we lead in today’s society. We are often bombarded with information, expectations and responsibilities which can take a toll over time.



The first step of overcoming overwhelm is acknowledging the feeling


Identifying the specific cause of overwhelm is an important first step. It is also worth noting that each person has a different threshold for stress as everyone handles stress in their own way. What overwhelms one person may not bother the next. The key is to acknowledge your feelings followed by taking practical steps to manage it.



Let go of control;


Focus on what you can control as focusing on what we have no control over increases anxiety. It can be helpful to try to redirect your attention to something within your control and practice letting go of the uncontrollable.



Implement strategies to manage the feelings of overwhelm;


Another important element to dealing with overwhelm is implementing practical strategies to manage it. These can include prioritizing tasks, taking breaks and practicing mindfulness. It is also important to prioritize self-care practices like exercise, healthy eating habits and getting enough sleep which can help build resilience and improve your ability to cope with stress.



Learn to say "no" and set healthy boundaries;


This is also a fundamental aspect of dealing with feelings of overwhelm. By setting boundaries you are not rejecting others or being selfish, as boundaries help other people know what you need and expect. It is also important to find a healthy outlet for emotions by talking to someone you trust or writing on a journal.



To your question about the difference between experiences of stress, anxiety or depression;


These experiences are distinct yet interconnected mental health experiences. The similarities between the symptoms of stress, anxiety and depression can make it challenging to identify what is being experienced. It is important to note, while stress is normal, symptoms of severe


depression and anxiety (such as panic attacks and profound sadness) can disrupt daily activities and the overall quality of life.


If you are still unsure which one of these three you are experiencing and if feelings of overwhelm has begun to significantly impact your ability to function, consider seeking professional help from a therapist or counsellor.


Amharic version to follow below.







ree

ምላሽ ከቤት ውስጥ ቴራፒስት፡


ውድ አንባቢ፡


ስላደረሡን እናመሠግናለን።


ዕርዳታ የሚያሥፈልገን መሆኑን መቀበል ድፍረት ይጠይቃል። የመጨናነቅ ስሜት ሁለንተናዊ የሰው ተለምዶ ነው። ይህ ልምድ በዛሬው ማሕበረሠብ ውስጥ በምንመራው ፈጣን ዘመናዊ ህይወት የተነሣ ይባባሣል። በየጊዜው የሚዘንቡብን መረጃዎች፡ የሚጠበቁብን ነገሮችና ኃላፊነቶች ውርጅብኝ ከጊዜ ብዛት ጉዳት ሊያደርሡብን ይችላሉ።



መጨናነቅን ለመወጣት የመጀመሪያው ዕርምጃ ለሚሠማን ስሜት ዕውቅና መሥጠት ነው።


የመጨናነቅን ልዩ መንሥዔ መለየት ጠቃሚ የመጀመሪያ ዕርምጃ ነው። እያንዳንዱ ሰው ጭንቀትን የሚያስተናግደው በራሱ መንገድ እንደመሆኑ፡ ለጭንቀት የተለያየ ገደብ እንዳለውም ልብ ማለትን ያሻል። አንዱን ሰው የሚያጨናንቀው ጉዳይ ሌላውን ላይረብሸው ይችላል። ቁልፉ ለስሜቶችዎ ዕውቅና መሥጠትና ያንንም ተከትሎ መልክ ለማስያዝ ተግባራዊ ዕርምጃዎችን መውሠድ ነው።



ለቀቅ ማድረግ


መቆጣጠር በማንችለው ላይ ማተኮር ሥጋትን ስለሚጨምር፡ መቆጣጠር በሚችሉት ላይ ትኩረት ያድርጉ። ትኩረትዎን በቁጥጥርዎ ውስጥ ወዳለው መቃኘትና የማይቆጣጠሩትን ለቀቅ ለማድረግ መለማመድ ሊረዳ ይችላል።



የመጨናነቅን ስሜቶች በወጉ ለመያዝ ሥልቶችን ይተግብሩ።


መጨናነቅን መላ ለማለት ሌላው ጠቃሚ መሠረታዊ ነገር ተግባራዊ ሥልቶችን በሥራ ላይ ማዋል ነው። እነዚህም፡ ሥራዎችን እንደ ቅድሚያቸው ማበላለጥ፡ ዕረፍቶችን መውሠድና ራስን ተኮርነትን መለማመድን ሊያካትቱ ይችላሉ። እንዲሁም ተቋቋሚነትን ለመገንባት የሚረዱና ጭንቀትን የመጋተር ችሎታዎን የሚያሻሽሉትን፡ የሰውነት ዕንቅስቃሴ መሥራት፡ ጤነኛ የአበላል ልምዶችንና በቂ ዕንቅልፍ ማግኘትን በመሣሰሉት ለራስ ጥንቃቄ ቅድሚያ መሥጠት ጠቃሚ ነው።



አይሆንም ማለትን መማርና ጤነኛ ድንበርን ማበጀት የመጨናነቅን ስሜቶች መላ የማለት መሠረታዊ ገፅታ ነው።


ገደቦች እርስዎ የሚፈልጉትንና የሚጠብቁትን ሌሎች ሰዎች እንዲያውቁ ስለሚረዳ፡ ድንበር ማበጀትዎ፡ ሌሎችን አለመቀበልዎ ወይም ንፉግ መሆንዎ አይደለም። ደግሞም ለሆነ ለሚያምኑት ሰው በማውራት ወይም ማስታወሻ ላይ በመፃፍ፡ የውስጥ ነውጥዎን የሚያወጡበት ጤናማ መተንፈሻ ማግኘት ጠቃሚ ነው።



በጭንቀት፡ በሥጋትና በድብርት መካከል ስላለው ልዩነት ለጠየቁት ጥያቄ፡


እነዚህ ልምምዶች ልዩና ነገር ግን የተያያዙ የአዕምሮ ጤና ልምምዶች ናቸው። የጭንቀት የሥጋትና የድብርት ምልክቶች መመሣሰል፡


በወቅቱ ምን እየተሠማ እንደሆነ መለየቱን አስቸጋሪ ሊያደርገው ይችላል። ጭንቀት የተለመደ ሲሆን፡ የከፋ ድብርትና ሥጋት (ድንገተኛ የመረበሽ ስሜትና መሪር ሀዘን)፡ ዕለታዊ ዕንቅሥቃሴና አጠቃላይ ጥራተ ሕይወትን ሊያስተጉጉሉ ይችላሉ።



ከእነዚህ ከሦስቱ ውስጥ የሚሠማዎ የትኛው እንደሆነ ዕርግጠኛ ካልሆኑና የመጨናነቅ ስሜቶች የመተግበር ችሎታዎ ላይ ጉልህ ተጽዕኖ ማሣደር ከጀመሩ፡ ከወጌሻ ወይም ከአማካሪ የባለሞያ ዕርዳታ መፈለግን ያስቡበት።

 
 
 

Comments


bottom of page