top of page

Wisdom Well August 2024


ree

Dear reader,


The mother-daughter relationship is the most powerful relationship for a woman. A daughter’s relationship with her mother lays the foundation for her relationship with herself. As such, it is very important to nurture and cultivate the relationship. There is a lot that is not mentioned regarding your relationship with your daughter, including her age, so I will make some suggestions that have proven to be helpful for most mother-daughter relationships. 

I want to point out that the challenge you are facing is not unusual as many women have extremely complex relationships with their mothers. It is not uncommon for the relationship to break down, heal and transform over time. A large contributing factor to the conflict between mothers and daughters (especially for second generation Canadians) is not feeling heard and understood by the other. This leads to misunderstandings and sometimes resentment. 

Empathy and understanding are the building blocks of a healthy relationship between children and their parents. My suggestion is to start working towards building a relationship based on love and respect. It is also important to engage in meaningful conversations consisting of listening, problem solving and making suggestions for healthy changes. The steps you take to improve your relationship depends on the specific challenges you face, but here are some questions you can ask your daughter to start a meaningful conversation. As you engage with her responses, make sure to listen attentively, and use kind language that makes her feel respected and loved. 

  1. What has it been like being my daughter? 

  2. What do you most wish for in this relationship? 

  3. What kind of things would make you feel cared for? 

  4. What have you been thinking about lately? 


It is important to remember that children subconsciously pick up traits of their parents. These traits could be positive, like punctuality, honesty, and empathy, or children could mirror their parents’ negative traits such as dishonesty, disrespect and the likes. With that in mind, parents would do well to be mindful of their behaviour around their children. 

To conclude, my advice is to be empathetic, respectful and understanding while staying mindful of your own behaviour so as to ensure what is being mirrored back to you is what you like to see. In addition, it can also be helpful to attend a counselling session with your daughter to build a strong emotionally connected relationship. 


Amharic version to follow below.




ree

ውድ አንባቢ፡

 

የእናትና ልጅ ግንኙነት፡ ለሴት ልጅ እጅግ በጣም ጠንካራ ግንኙነት ነው:: ሴት ልጅ ከእናትዋ ጋር ያላት ግንኙነት፡ ከራስዋ ጋር ላላት ግንኙነት መሠረት ይጥላል። በመሆኑም፡ ግንኙነቱን መንከባከብና መኮትኮት በጣም ጠቃሚ ነው። ከልጅዎ ጋር ያለዎትን ግንኙነት በሚመለከት፡ ዕድሜዋን ጨምሮ ብዙ ያልተጠቀሠ አለ። ስለዚህም፡ ለብዙዎች የእናትና የሴት ልጅ ግንኙነቶች ጠቃሚነታቸው የተረጋገጠ አንዳንድ ምክረ ሃሣቦችን እሠጣለሁ።


ብዙ ሴቶች ከእናቶቻቸው ጋር በጣም የተወሣሰበ ግንኙነት ያላቸው እንደመሆኑ፤ ያጋጠመዎት ተግዳሮት ያልተለመደ እንዳልሆነ መጠቆም እፈልጋለሁ።


የግንኙነት መሠበር፣ በጊዜ መጠገንና መሻሻል ያልተለመደ አይደለም። በእናቶችና ሴት ልጆች መካከል ለሚፈጠረው አለመግባባት ትልቁን አስተዋጽፆ የሚያደርገው (በተለይም ለሁለተኛ ትውልድ ካናዳውያት) ሌላው ወገን አይሠማንምና አይረዳንም የሚለው ስሜት ነው። ይህም ወደ አለመግባባትና አንዳንዴም ወደ ቂም ያመራል።


ርህራሄና መረዳት፡ በወላጆች ወይም አሣዳጊዎችና ልጆች መካከል የጤነኛ ግንኙነት መገንቢያ ጡቦች ናቸው። የኔ አስተያየት በፍቅርና በአክብሮት ላይ የተመሠረተ ግንኙነትን ለመገንባት መሥራት ስለ መጀመር ነው። መሥማትን፤ ለችግር መፍትሔ መሥጠትና ለጤናማ ለውጥ አስተያየት መጋራትን የሚያካትቱ ትርጉም ያላቸው ውይይቶች ውስጥ መሣተፍም ጠቃሚ ነው። ግንኙነቱን ለማሻሻል የሚወስዷቸው ዕርምጃዎች እንደሚገጥሙዎት ተግዳሮቶች ሁኔታ ቢሆንም፤ ትርጉም ያለው ውይይት ለመጀመር ልጅዎን ሊጠይቋት የሚችሏቸው አንዳንድ ጥያቄዎች እኒሁልዎ። ምላሾቿን ሲያገኙ፡ በትኩረት ማዳመጥዎንና፣ መከበሯና መወደዷእንዲሠማት የሚያደርጋትን ደግ ቋንቋ መጠቀምዎን ያረጋግጡ።


፩፡ የኔ ልጅ መሆን ምን ይመሥላል?

፪፡ በዚህ ግንኙነት ውስጥ የበለጠ የምትመኚው ምንድን ነው?

፫፡ ጥንቃቄ እንደተደረገልሽ እንዲሠማሽ የሚያደርጉሽ ምን ዓይነት ነገሮች ናቸው?

፬፡ አሁን አሁን ላይ ምን እያሠብሽ ነበር?


ልጆች ሣያውቁት የወላጆቻቸውን ወይም የአሣዳጊዎቻቸውን ባህርያት እንደሚቀስሙ ማስታወስ ጠቃሚ ነው፤ እነዚህ ባህሪያት፡ አዎንታዊ: ማለትም እንደ ሰዓት አክባሪነት፣ ሀቀኝነትና ርህራሄ፡ ወይም ልጆች የወላጆቻቸውን ወይም አሣዳጊያቸውን አሉታዊ ባህሪያት፡ ማለትም እንደ ቃል አባይነት፣ ሰው አለማክበርና የመሣሰሉትን ሊያንጸባርቁ ይችላሉ። ይህን በማስተዋል፤ ወላጆች ወይም አሣዳጊዎች በልጆቻቸው አካባቢ የሚያሣዩትን ዓመል ልብ ቢሉ መልካም ይሆናል።


ለማጠቃለል የኔ ምክር ተመልሶ ወደ እርስዎ የሚንጸባረቀው ማየት የሚወዱት መሆኑን ለማረጋገጥ፡ ሁሌም የራስዎን ዓመል ልብ የሚሉና ሩህሩህ፣ ሰው አክባሪና መረዳት ያለዎ እንዲሆኑ ነው። በተጨማሪም፡ ከልጅዎ ጋር የማማከር አገልግሎት ቢከታተሉ ጠንካራ በመንፈስ የተገናኘ ግንኙነት ለመገንባት ሊረዳ ይችላል።


 
 
 

Comments


bottom of page